Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር ለሕዳሴ ግድብ የ2 ነጥብ 7 ሚሊየን የጅቡቲ ፍራንክ ቦንድ ግዢ ፈጸመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የ2 ነጥብ 7 ሚሊየን የጅቡቲ ፍራንክ ቦንድ ግዢ ፈጽሟል፡፡

የማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ አመራሮች በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በተገኙበት የቦንድ ግዢውን አስረክበዋል።

ኮሚዩኒቲው ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ለሚደረጉ የተለያዩ የልማት ጥሪዎች እና ማህበራዊ ድጋፎች ሕዝቡን በማስተባበር ትልቅ ተሳትፎ ሲያደርግ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

አሁን ላይም የ2 ነጥብ 7 ሚሊየን የጅቡቲ ፍራንክ የቦንድ ግዥ በመፈጸም ድጋፋቸውን ማሳየታቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version