Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የዲጂታል ትኬት ሽያጭ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በተመረጡ የትኬት መቁረጫ ጣቢያዎች የዲጂታል የትኬት ሽያጭ በሙከራ ደረጃ እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡

የዲጂታል የትኬት ሽያጩ፤ በዳግማዊ ምኒልክ፣ ጦር ኃይሎች፣ ሀያት፣ ስታዲየም እና ቃሊቲ መሥመሮች በሙከራ እንደሚጀመር የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርሃን አበባው (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

የባቡር ትኬት መቁረጫ ሱቆች ከባቡር ጣቢያዎች የራቁ በመሆናቸው ትኬት ለመግዛት ያሉ እንግልቶችን ለማስቀረት ሲባል አገልግሎቱን ዲጂታላይዝ ማድረግ አስፈልጓል ብለዋል፡፡

ተገልጋዮች በቴሌ ብር በኩል ትኬት መቁረጥ እንደሚችሉ ጠቅሰው፤ ሞባይል ለሌላቸው ተገልጋዮች የወረቀት ትኬት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት በ19 ባቡሮችና በ39 የትኬት መቁረጫ ጣቢያዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በመሳፍንት እያዩ

Exit mobile version