የሀገር ውስጥ ዜና

የሪል ስቴት ልማትንና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይት ግመታን ለማስፈፀም የሚያስችል ረቂቅ ደንብ ተዘጋጀ

By abel neway

March 12, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሪል ስቴት ልማትንና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታን ግልጽና ወጥ በሆነ መንገድ ለመምራት የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀቱን የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡

የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ሔለን ደበበ በሪል ስቴት አልሚዎች የሚቀርቡ ቤቶች የአብዛኛውን የከተማ ነዋሪ የቤት ፍላጎት መመለስ እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ሂደት የዜጎችን የቤት ፍላጎት ለማሟላት እና ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችን በተመጠጣኝ ዋጋ ማቅረብ የሚያስችል ሴክተሩን የሚደገፍ የህግ ማዕቀፍ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ገልፀዋል፡፡

አሁን የቀረበው የህግ ማዕቀፍ በቤት ልማት ሂደቱ እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይት ግመታ ላይ የነበሩ ብልሹ አሰራሮችን በማስተካከል ማህበረሰቡም ሆነ መንግስት ከዘርፉ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኙ ያስችላል ብለዋል፡፡

በመሆኑም በክልልና በከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ አስፈፃሚ አካላት የሪል ስቴት ልማትና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ የህግ ማዕቀፍን ለማስፈፀም በቁርጠኝነት መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

በቤዛዊት ከበደ