የሀገር ውስጥ ዜና

ፈረንሳይ መከላከያ ዋር ኮሌጅ እያበረከተ ያለውን አስተዋፆኦ አደነቀች

By abel neway

March 12, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጄኔራል ስቴፈን ሩሽ የተመራ የፈረንሳይ መከላከያ ልዑክ የመከላከያ ዋር ኮሌጅን ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱ ወቅትም፤ የመከላከያ ዋር ኮሌጅ በዓለም አቀፋዊና ቀጣናዊ ትሥሥር እያበረከተ ያለውን ጉልህ አስተዋፆኦ ልዑኩ አድንቋል፡፡

ኮሌጁ ወታደራዊ ስትራቴጂክ አመራር እንዲፈጠር ከኢትዮጵያ አልፎ ለአካባቢው ሀገራት ዐቅምን በመገንባት በመማር ማስተማር ሂደት ያበረከተው ጉልህ ሚና የሚበረታታና የሚደገፍ ነው ብሏል፡፡

የኮሌጁ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ቡልቲ ታደሠ በበኩላቸው፤ የመማር ማስተማር ሂደትን በተመለከተ በመደጋገፍ ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እና ተግባቦት በመፍጠር ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ይህን ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡