የሀገር ውስጥ ዜና

በሸካ ዞን ፊዴ ከተማ ዛፍ ወድቆ የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

By Adimasu Aragawu

March 13, 2025

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሸካ ዞን ፊዴ ከተማ ትልቅ ዛፍ ወድቆ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡

በገበያ መሃል በደረሰው አደጋ ከሟቾች በተጨማሪ በ8 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡

የክልሉ መንግስት በአደጋው በደረሰው ሞትና ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፡፡