የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአንጎላ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Adimasu Aragawu

March 13, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአንጎላ ፕሬዚዳንት ጆኣኦ ሎሬንቾ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው፥ “የአንጎላ ፕሬዚዳንት ጆኣኦ ማኑኤል ጎንካልቬስ ሎሬንቾን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጡ እላለሁ” ብለዋል።

በውይይታቸውም ፕሬዚዳንቱ በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበርነታቸው ቁልፍ አኅጉራዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል።