ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነገ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ

By Melaku Gedif

March 19, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በነገው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።

በፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርትን መነሻ በማድረግ ከም/ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡