አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ ሕብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በሶማሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ ለማኅበራዊ ችግር ተጋላጭ የሕብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉ የተደረገው በደቡባዊ ሶማሊያ ጌዶ ክልል ባርዴሬ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሰዎች ነው፡፡
የሠራዊቱ አባላት ከጸጥታ ሥራዎች ባለፈ ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ በቀጣናው የሚገኘው ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ሞላ ሹመት አረጋግጠዋል፡፡
የባርዴሬ ዲስትሪክት ኮሚሽነር ኢስማኤል ሼክ አብዲ የኢትዮጵያ ሠራዊት ላደረገው ድጋፍ ምሥጋና ማቅረባቸውን ከተልዕኮው ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡