አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት የቅድመ ዝግጅት ሥራ ከ80 በመቶ በላይ መጠናቀቁን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
6 ሺህ ተሳታፊዎች የሚጠበቁበት የክልሉ የአጀንዳ ማሰባሰብ በቅርቡ በባሕር ዳር ከተማ እንደሚካሄድ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል።
የክልሉ ሕዝብ ለሀገራዊ ምክክሩ ዝግጅት አድርጎ እየተጠባበቀ መሆኑንም ተገንዝበናል ብለዋል፡፡
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በምክክሩ እንዲሳተፉም ጠይቀዋል፡፡
ኮሚሽኑ በጎንደር፣ ባሕር ዳር፣ ደሴ እና ደብረ ብርሃን ክላስተሮች በዞንና በወረዳ ደረጃ የተሳታፊ ልየታ ማከናወኑ ይታወሳል።
በርስቴ ፀጋዬ