ስፓርት

በ1 ሺህ 500 ሜትር ጉዳፍ ጸጋይና ድርቤ ወልተጂ ለፍጻሜ አለፉ

By Hailemaryam Tegegn

March 21, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ጉዳፍ ጸጋይና ድርቤ ወልተጂ ለፍጻሜ አለፉ፡፡

በቻይና ናንጂንግ እየተካሄደ በሚገኘው ሻምፒዮና፥ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተሳተፉበት የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ተካሂዷል፡፡

በምድብ 1 የተሳተፈችው አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በ4 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ ከ87 ማይክሮ ሰከንድ 1ኛ በመውጣት ለፍጻሜ ማለፍ ችላለች፡፡

በምድብ 3 የተሳተፈችው ሌላኛዋ አትሌት ድርቤ ወልተጂ ደግሞ በ4 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ ከ25 ማይክሮ ሰከንድ በተመሳሳይ 1ኛ በመውጣት ፍጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡