Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ምክንያታዊነት በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት …

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክንያታዊነት በአንድ ሀገር ውስጥ ለሚከናወን የሰላም ግንባታ እና የምክክር ሂደት ዋነኛውን ሚና ይጫወታል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተቋቋመበት የመመስረቻ አዋጅ ላይ ምክንያታዊነት ከሀገራዊ ምክክሩ መርሆዎች አንዱ ተደርጎ መደንገጉም ይታወቃል፡፡

ጽንሰ-ሐሳቡ በምክክር ሂደት ውስጥ በምን አግባብ ጥቅም ላይ እንደሚውል ማወቅ እንደሚገባ ኮሚሽኑ በማኅበራዊ ትሥሥርገጹ አጋርቷል፡፡

በሀገራዊ ምክክር ዐውድ ውስጥ ምክንያታዊነት፤ ከስሜታዊነት፣ ከጥላቻ እና ከሐሳብ ግትርነት የፀዳ፤ አመክንዮን እና ማስረጃን መሰረት ያደረገ ውይይትን እና ውሳኔዎችን ለማሳለፍ የሚያግዝ የሥነ-ምግባር መርህ ይላል ኮሚሽኑ፡፡

ይህም ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ የጋራ መፍትሔን ለመፈለግ የሚያደርጉትን በጎ ጥረት ያጠናክራል ሲል ገልጿል፡፡

ይህንን መነሻ በማድረግ ምክንያታዊነት በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ እንዴት ተፈፃሚ እንደሚሆን የሚከተሉትን ሐሳቦች ይዘረዝራል፡-

አመክንዮን እና ማስረጃን መሰረት ማድረግ

በዚህ ሂደት ዜጎች እና ባለድርሻ አካላት ከስሜታዊነት እና ጥላቻ በፀዳ አኳኋን በውይይቶች ላይ ተሳትፎን እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ገለልተኝነትን እና ፍትሐዊነትን መሰረት ማድረግ

ምክንያታዊ በሆነ የሀገራዊ ምክክር ሂደት ሚዛናዊ የሆኑ ውይይቶች እንዲደረጉ ከማገዙም በላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ድምፆቻቸው በእኩልነት እንዲሰሙ በር ከፋች ነው፡፡

በሰው ልጆች እኩልነት ማመንን ማበረታታት

በኢትዮጵያ የሚደረጉ የሀገራዊ ምክክር ሂደቶች የሰው ልጆች በጋራ ችግሮቻቸው ላይ የሚወያዩባቸው እንደመሆናቸው መጠን፤ የሰው ልጀችን እኩልነት እና ተፈጥሯዊ ማንነት ማክበር ይኖርባቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!

Exit mobile version