አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እስከ ትናንት ድረስ 964 ሺህ 118 ነጥብ 1 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ከዚህ ውስጥም 836 ሺህ 253 ነጥብ 2 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን እና 127 ሺህ 864 ነጥብ 9 ሜትሪክ ቶን ደግሞ በወደብ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡
ወደ ሀገር ውስጥ ከተጓጓዘው መካከልም 523 ሺህ 375 ነጥብ 2 ሜትሪክ ቶን ዳፕ እንዲሁም 312 ሺህ 878 ሜትሪክ ቶን ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡