Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ገዢ ትርክት የልማት ተነሳሽነት፣ የአብሮነት እና የወንድማማችነት ትስስር ይፈጥራል – ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰባሳቢ ትርክት የሰዎችን አብሮነት፣ የማንነት እሴት እንዲጎለብት ያግዛል ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ገልጸዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል “ውጤታማ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ለገዢ ትርክት” በሚል መሪ ሃሳብ ለሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በስልጠናው ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ ገዢ ትርክት የሀገር ታሪክ የወደፊት ተስፋ እና ዛሬ ላይ የሚኖረውን ሚና የሚከስቱ ክስተቶችን የምንመለከትበት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አሰባሳቢ ትርክት የሰዎችን አብሮነት፣ የማንነት እሴት እንዲጎለብት እንደሚያግዝ አንስተው፤ ገዢ ትርክት በህዝብ ውስጥ የላቀ የልማት ተነሳሽነት፣ የአብሮነት እና የወንድማማችነት መልካም ትስስር እንደሚፈጥር አመላክተዋል።

የሀገሪቱን የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወሰነው በትርክት ስለመሆኑ እና የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ዘርፉ ይህን በማጉላት የህዝቡ አብሮነት እና መልካም እሴቶች እንዲጎለብቱ ማገዝ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በስልጠናው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊና የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ፣ የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቱ እና ሌሎች አመራሮች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

Exit mobile version