Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምራቾች በጉሙሩክ አሰራር የሚያጋጥማቸውን ችግር ለመፍታት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን በጉምሩክ አሰራር ዙሪያ ከአምራች ድርጅቶች ጋር እየተወያየ ነው፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷አምራች ድርጅቶች ለሚገጥሟቸው ችግሮች ምላሽ በመስጠት በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ያላቸውን አበርክቶ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

አምራች ዘርፉን ለማበረታታት የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመው ÷ በተለይም የኢኮኖሚ ሪፎርም ማሻሻያው አበረታች ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ አሰራሩን በቴክኖሎጂ በማስደገፍና ፖሊሲዎችን ለማሻሻል ያከናወናቸው ተግባራት ተጠቃሽ መሆናቸውን አንስተዋል።

የተሻሻለው ፖሊሲ በዋናነት ፍትሃዊና ተአማኒ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ አሰራሮችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዝ ነው ብለዋል።

እንዲሁም የድንበር ቁጥጥርን ለማጠናከርና ቴክኖሎጂያዊ አሰራሮችን ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል መሆኑን ነው የጠቀሱት፡፡

ኮሚሽኑ አሰራሩን ከማዘመንና ከማሻሻል በዘለለ ከአምራች ድርጅቶች ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር ሌላኛው የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም የቀረጥ፣ የግብር እፎይታና መሰል ተግባራት አምራች ድርጅቶችን ለማበረታታት የሚከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል።

Exit mobile version