የሀገር ውስጥ ዜና

በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አተገባበር ላይ የሚመክር መድረክ በባህር ዳር እየተካሄደ ነው

By abel neway

March 25, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አተገባበር ላይ የሚመክር የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሸነር መኩሪያ ሃይሌን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የዞንና የከተማ አሰተዳደር አመራሮች ተሳትፈዋል።

“ሲቪል ሰርቪሱ ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከናወነ የሚገኘው የንቅናቄ መድረክ ነፃና ገለልተኛ ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት ቀልጣፍና ዘመናዊ አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ እርካታን ለማረጋገጥ የሚያግዝ መሆኑ ተመላክቷል።

መድረኩም የመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም እና በአንድ ማዕከል አገልግሎት አተገባበር ዙሪያ በሚቀርቡ ሰነዶች ላይ በመምከር የቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዘገበው ኢዜአ ነው።