የሀገር ውስጥ ዜና

የሙስና ወንጀል ህግ የማስከበር ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ አሰራርን ማዘመን ያስፈልጋል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

By Melaku Gedif

March 25, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሙስና ወንጀል ህግ የማስከበር ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራርን ማዘመን አስፈላጊ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ ዛሬ የሙስና ወንጀል ሕግ የማስከበር ሥራዎች የባለድርሻ ተቋማት የምክክር መድረክ አካሂደናል ብለዋል።

በውይይቱም የባለድርሻ አካላቱ ቅንጅታዊ አሰራርና የስራ አፈጻጸም ምን እንደሚመስል ምክክር መደረጉን ገልጸዋል።

ተቋማቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ቅንጅታዊ አሰራርን በማዘመን፣ በፀረ-ሙስና ትግል ሀገራዊ የጋራ ተልዕኮን ማዕከል በማድረግ የሚያከናውኗቸውን ተግባራት አጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ መቀመጡን አመልክተዋል።