የሀገር ውስጥ ዜና

የኮሪደር ልማት ሥራ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው የመዲናዋ ነዋሪዎች ተናገሩ

By abel neway

March 26, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ምቹ ሁኔታዎችን እንደፈጠሩላቸው ነዋሪዎች ተናገሩ።

ከአፍንጮ በር እስከ ፒኮክ መናፈሻ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ አስመልክቶ ሐሳባቸውን ያካፈሉ የመዲናዋ ነዋሪዎች እንዳሉት፤ በመንገዶች ላይ ውብ ገፅታን ከመፍጠር ባሻገር የእግረኛ መንገዶች መስፋት ለማንበብ እንዲሁም ለመዝናናት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡

ከተማን ማስዋብ አንድ የእድገት ማሳያ ነው የሚሉት ነዋሪዎቹ፤ ከዚህ በፊት ለመዝናናት እራቅ ወዳለ ስፍራ ለማምራት ይገደዱ እንደነበር አውስተዋል፡፡

አሁን ላይ ግን በአቅራቢያችን ባሉ በርካታ የኮሪደር ልማቶች፤ የመዝናኛ፣ የማንበቢያ እና ማረፊያ ሥፍራዎችን ማግኘታቸውን እና ይህም እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም በሁሉም ስፍራዎች የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች ተጠናቀው፤ መዲናዋ በይበልጥ እንደምትዋብና ለነዋሪዎቿም ይሁን ለእንግዶች ምቹ እንደምትሆን ያላቸውን ተስፋ አመላክተዋል፡፡

በመቅደስ ከበደ