Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የእንግሊዝ ኩባንያዎች በኢኮኖሚ ማሻሻያው የተፈጠረውን ምቹ ዕድል እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ የተፈጠረውን ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል እንዲጠቀሙበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ፡፡

በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት የተዘጋጀው የኢትዮጵያና እንግሊዝ የቢዝነስ ፎረም በለንደን ተካሂዷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ በዚሁ ወቅት፥ በኢትዮጵያ የተከናወኑ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የፈጠሩትን ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል የእንግሊዝ ኩባንያዎች እንዲጠቀሙበት ጥሪ አቅርበዋል።

በፎረሙ ላይ በርካታ የእንግሊዝ ኩባንያዎች የተሳተፉ ሲሆን፥ በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችና የመንግሥት ፖሊሲዎች ዙሪያ ገለጻ መደረጉን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Exit mobile version