Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር በቡና ዘርፍ ትብብሯን ማጠናከር እንደምትፈልግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ ጋር በቡና ዘርፍ ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን አስታወቀ።

ጣሊያን የግሉ ዘርፍ በኢትዮጵያ የቡና ልማት ውስጥ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ ከሀገር በቀል አምራቾች ጋር በማስተሳሰር ሙያዊ ድጋፍ የመስጠት ፍላጎት እንዳላት የኤጀንሲው ዳይሬክተር ሚሼል ሞራና ገልጸዋል፡፡

በጣሊያን መንግሥት ድጋፍ እየየተገበረ የሚገኘው የኢትዮጵያ የቡና ዘርፍ የእሴት ሰንሰለትን የማጠናከር ፕሮጀክት ውጤቶች እየተገኙበት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ከፈረንጆቹ 2006 ጀምሮ በኢትዮጵያ የቡና ልማት የእሴት ሰንሰለት መፍጠር ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል፡

Exit mobile version