አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ እና የአፋር ክልሎች ህዝቦች የሰላም እና የልማት ፎረም ተመሰረተ።
የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች የወንድማማችነት ግንኙነት ማጠናከሪያ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታዎች ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) እና ቸሩጌታ ገነነ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።
የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ፎረሙ የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች ለጋራ ሰላም እና አንድነት የሚሰሩበት ነው።
እንዲሁም በጋራ እሴቶቻቸው እና የወንድማማችነት ግንኙነትን ለማጠናከር የሚመክሩበት መሆኑን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።