የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያን የዕዳ ሽግሽግ ጥረት በተመለከተ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ገለጻ ተደረገ

By Hailemaryam Tegegn

March 26, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የዕዳ ሽግሽግ እንዲደረግ እያከናወነቻቸው ያሉትን ተግባራት በተመለከተ የገንዘብ ሚኒስቴር ለዋና ዋና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ገለጻ አድርጓል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፥ ተቋማቱ ከኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ ጋር በተጣጣመ ሁኔታ በቀጣይ ለሚከናወኑ ድርድሮች እንዲዘጋጁ አሳስበዋል፡፡

በቅርቡ ከኢትዮጵያ የአበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር ከስምምነት መደረሱ የተገለጸ ሲሆን፥ የኢትዮጵያ የዕዳ ሽግሽግ ጥረት በጥሩ ሂደት ላይ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡