የሀገር ውስጥ ዜና

የሕዳሴው ግድብ የተስፋ፣ የይቻላል እና የማድረግ አቅም ማሳያ ነው- ተማሪዎች

By ዮሐንስ ደርበው

March 26, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተስፋ፣ የይቻላል እና የማድረግ አቅም ማሳያ መሆኑን ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ያነጋገራቸው ተማሪዎች ገለጹ፡፡

ግድቡ ያለፈባቸው ተግዳሮቶች እና አሁን የደረሰበት የድል ብስራት ጉዞ ለነገው ትውልድ ማሳያ መሆኑንም ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተስፋ፣ የይቻላል እና የማድረግ አቅም ማሳያ መሆኑን ገልጸው፤ ሀገር ከእነርሱ ለምትጠብቀው ሥራ ተምሳሌት እንደሚያደርጉት አንስተዋል፡፡

የሕዳሴው ግድብ የሥራ ሂደት ነገ ለሚኖረው ጉዞ መሠረት ሆኖ የማገልገል አቅም እንደሚፈጥር የገለጹት ደግሞ የሥነ-ልቦና ባለሙያ የሆኑት ተስፋዬ አሰፋ ናቸው፡፡

አድርጎ የማሳየት፣ ጀምሮ የመጨረስ ማሳያ የሆነው ግድቡ ቀጣዩ ትውልድ ሊከውናቸው ለሚችሉ ተግባራት መነሻ ተሞክሮ ይሆናል ነው ያሉት፡፡

ሀገሪቱን የሚረከበው የነገው ትውልድም ፈተናዎችን ድል የመንሳት ጥበብ ከዚህ ፕሮጀክት ሂደት ተምሯል ብለዋል፡፡

በሚኪያስ ዓለሙ