የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By ዮሐንስ ደርበው

March 26, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቭርሃም ንጉሤን (ዶ/ር) በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ውይይታቸው የኢትዮጵያን እና የእስራኤልን ትብብር በይበልጥ ማጠናከር ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

አምባሳደሩ ከፕሬዚዳንት ታዬ ጋር የነበራቸውን ውይይት በተመለከተ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በምክክራችን የኢትዮጵያ እና እስራኤል ግንኙነት ልዩ፣ ጥልቅ እና ታሪካዊ መሆኑን አንስተናል።

ሁለቱ ሀገራት በኢኮኖሚ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በደን ልማት፣ በቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በሞደርናይዜሽን እና በጤና ዘርፎች በትብብር እየሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በቁርጠኝነት እንደምትሰራም ነው ያረጋገጡት፡፡