Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሐረር ኮሪደር ልማት የኤሌክትሪክ መስመር ማዛወር ሥራ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐረሪ ከተማ የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት የመካከለኛና ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ማሰራጫ መስመር ማዛወርና ማሻሻያ ሥራ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ በአጠቃላይ 1 ሺህ 107 የእንጨትና የኮንክሪት ምሰሶዎች፣ 40 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኤሌክትሪክ መስመር እንዲሁም 12 የተለያየ መጠን ያላቸው ትራንስፎርመሮችን የማዛወር ሥራ ማከናወኑ ተጠቁሟል፡፡

የመስመር ማዛወር ሥራው በሐረር ከተማ ከ4ኛ እስከ ስታዲየም፣ ከአጅፕ እስከ ሰላም አደባባይ፣ ከሐረር ቢራ እስከ ገስታውስ፣ ከ4ኛ እስከ ቀይ መስቀል እንዲሁም ከኢማም አህመድ ስታዲየም እስከ ገስታውስ የሚሸፍን መሆኑ ተገልጿል፡፡

በቀጣይ በ2ኛው ዙር በሚከናወነው የኮሪደር ልማት 1 ነጥብ 66 የመካከለኛ እና 2 ነጥብ 45 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ መስመር የማዛወር ሥራ እንደሚከናወን የተቋሙ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version