Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፊቼ ጫምባላላ በዓል ዋዜማ “ፊጣሪ ሃዋሮ” በሀዋሳ መከበር ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል ዋዜማ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡

“ፊጣሪ ሃዋሮ” በመባል የሚታወቀው ክብረ በዓሉ በሲዳማ ባህል አዳራሽ እየተከበረ ሲሆን÷ በመርሐ-ግብሩ ላይ ሲፖዚየም፣ የፓናል ውይይቶችና የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚካሄዱ ተገልጿል፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድን ጨምሮ በርካታ እንግዶች በበዓሉ ላይ ለመታደም ሀዋሳ መግባታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Exit mobile version