አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሲዳማ ዘመን መለወጫ – ፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የሲዳማ ውብ ባህል መገለጫ የሆነው የፍቼ ጫምባላላ በዓል ፍቅር፣ እርቅ፣ ሰላም፣ ምስጋና እንዲሁም ብሩህ ተስፋ የሚሰነቅበት የዘመን መለወጫ በዓል መሆኑን አንስተዋል፡፡
በዓሉ ይበልጥ አንድነቱ የሚጠናከርበት፣ እርቅ፣ ሰላም፣ አብሮነት እና ብሩህ ተስፋ የሚሰነቅበት እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡