የሀገር ውስጥ ዜና

ፊቼ ጫምባላላን ከቱሪዝም መስኅቦች ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባ ተመላከተ

By Mikias Ayele

March 28, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፊቼ ጫምባላላ በዓልን ከሲዳማ ክልል የቱሪዝም መስኅቦች ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ አስገነዘቡ፡፡

የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ የሆነው የፊቼ ጫምባላለ በዓል አከባበር በሐዋሳ ጉዱማሌ እየተከናወነ ነው፡፡

በዚሁ ወቅት ሚኒስትሯ እንዳሉት፤ ከበርካታ የማይዳሰሱ ቅርሶቻችን መካከል ፊቼ ጫምባላላ አንዱ ነው፡፡

ይህን በዓልም ከሲዳማ ክልል በርካታ የቱሪዝም መስኅቦች ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆን መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡

በብርሃኑ በጋሻው