የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ያላቸውን ዘርፈብዙ ትብብር ለማጠናከር መከሩ

By Mikias Ayele

March 28, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እና የደቡብ ሱዳን የገንዘብ ሚኒስትር እና ተጠባባቂ የነዳጅ ሚኒስትር ማሪያን ዶንግሪን (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም፤ የሁለቱን ጎረቤት ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት ሊያሳድጉ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም የሀገራቱን የሁለትዮሽ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ሀገራቱን በመሠረተ ልማት፣ በኢነርጂ እና ሌሎች የልማት ዘርፎች ለማስተሳስር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይም ተወያይተዋል፡፡

ለዘላቂ ቀጣናዊ ሰላምና ፀጥታ ቅድሚያ ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባም በሁለቱ ወገኖች አፅንዖት ተሰጥቶታል፡፡