Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዚምባቡዌ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ ወዳጅነት ለማጠናከር ቁርጠኛ ናት – የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19፣2017(ኤፍ ኤም ሲ)፦ ዚምባቡዌ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ወዳጅነት ለማጠናከር እንደምትሰራ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ገለጹ።

በዚምባቡዌ የኢትዮጵያ አምባሳደር ራሽድ ሙሐመድ በሃራሬ የፕሬዚዳንቱ የአዲስ ዓመት መልዕክት ላይ ተገኝተዋል።

በዚሁ ወቅት ከዚምባቡዌው ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ጋር ተወያይተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያ እና ዚምባቡዌ ለረጅም ጊዜ ፀንቶ የቆየው የሁለትዮሽ ትብብር እንዳላቸው ገልፀዋል።

ይህም የበለጠ እንዲጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን በሃራሬ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

አምባሳደር ራሽድ ሙሐመድ የዚምባቡዌ መንግስት የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲጠናከር እያደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነዋል።

በመጪው ሚያዚያ ወር በሀገሪቱ በሚደረገው የዚምባቡዌ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢት እና ባዛር ላይ ከ10 በላይ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉ እና የሀገራቸው ምርት እንደሚያስተዋውቁ ከፕሬዝዳንቱ ጋር በነበራቸው ቆይታ ጠቁመዋል።

Exit mobile version