አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስድስተኛ ዙር ሰልጣኝ ዲፕሎማቶችን ስልጠና በዛሬው ዕለት አስጀምሯል።
በመርሐ ግብሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ስልጠናው ለቀጣይ 4 ወራት በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጥ ሲሆን÷ሰልጣኞች በቆይታቸው የፖሊሲ፣ የአካዳሚክና ተግባር ተኮር ስልጠናዎች እንደሚወስዱ ተገልጿል።