Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከአማራ ክልል ባለድርሻ አካላት ተወካዮች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል በሚያካሂደው የአጀንዳ ማሰበሰብ የምክክር ምዕራፍ ላይ ከሚሳተፉ ባለድርሻ አካላት ተወካዮች ጋር ተወያይቷል።

በመድረኩ ላይ ስለ ምክክር ምንነት፣ ዓላማ እንዲሁም በአጀንዳ ልየታና ማሰባሰብ ሂደት ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ባለድርሻ አካላቱ አጀንዳቸውን በሚያጠናክሩበት ስነ-ዘዴ ዙሪያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

የክልሉ የምክክር ባለድርሻ አካላት ተወካዮች ከሚያዚያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከወረዳ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በመሆን አጀንዳቸውን ማደራጀት እንደሚጀምሩ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version