የሀገር ውስጥ ዜና

117 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Hailemaryam Tegegn

April 02, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 117 መደበኛ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች በዚህ ሣምንት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

እነዚህ ወገኖች ወደ ሀገራቸው የተመለሱት ኤምባሲው እና ጅቡቲ የሚገኘው የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት በትብብር ባከናወኑት ሥራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚሁ መሠረት በሁለት ዙር በባቡር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ መደረጉን የኤምባሲው መረጃ አመላክቷል፡፡