አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቀጣይ የምክክር ምዕራፎች ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት÷በዛሬው ዕለት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የተደረገው ውይይት ለ9ኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ሀገራዊ ምክክሩን አካታች ለማድረግ ፖለቲካ ፓርቲዎችን በስፋት ማሳተፍ እንደሚገባ ገልጸው÷ፓርቲዎች ከኮሚሽኑ ጋር ተቀራርበው እየሠሩ በመሆናቸው አመስግነዋል፡፡
በመድረኩ ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) ባቀረቡት ጽሑፍ÷በእስካሁኑ ሒደት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በተከናወኑ ውይይቶች አንዱ የሌላውን ችግር እንዲረዳ ዕድል መፈጠራቸውን ተናግረዋል፡፡
ማንኛውም የፖለቲካ ኃይል በምክክር ሒደቱ ላይ መሳተፍ አለበት ያሉት ኮሚሽነር አምባዬ÷ ለዚህ ደግሞ ኮሚሽኑ የፓርቲዎችን ድጋፍ እንደሚፈልግ መግለጻቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡