Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኬቨን ዲብሮይን በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ማንቼስተር ሲቲን እንደሚለቅ ተረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቤልጂየማዊው የማንቼስተር ሲቲ የመሀል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዲብሮይን ከዘጠኝ ዓመት ቆይታ በኋላ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከቡድኑ ጋር እንደሚለያይ ተረጋግጧል፡፡

ተጫዋቹ ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ያለው ኮንትራት በውድድር ዘመኑ መጨረሻ የሚጠናቀቅ በመሆኑ በነፃ ዝውውር ማንቼስተር ሲቲን እንደሚለቅ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በክለቡ ቆይታው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ የተለያዩ ዋንጫዎችን ማሳካት የቻለው ኬቨን ዲብሮይን፤ በማንቼስተር ሲቲ ቤት በ412 ጨዋታ ተሰልፎ 106 ጎሎችን አስቆጥሯል።

174 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችንም አመቻችቶ አቀብሏል፡፡

ኬቨን ዲብሮይን ከማንቼስተር ሲቲ ጋር በውድድር ዓመቱ መጨረሻ እንደሚለያይ በማህበራዊ ትስስር ገፁ የገለፀ ሲሆን ደጋፊዎቹን አመስግኗል፡፡

የሳውዲ ክለቦች የተጨዋቹ ፈላጊ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን የተጫዋቹ ቀጣይ መዳረሻ የሳዑዲ አረቢያ ሊግ ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

Exit mobile version