Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአቡዳቢ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ባልደረቦች ለህዳሴው ግድቡ የ26 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአቡዳቢ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ባልደረቦች የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማጠናቀቂያ የድጋፍ ንቅናቄን በመቀላቀል የ26 ሺህ ዶላር ቦንድ ግዢ ፈጽመዋል::

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዑመር ሁሴን (ዶ/ር)፤ የቦንድ ግዢው የተከናወነው መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም 14ኛ ዓመቱን የያዘው ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ነው ብለዋል።

በአፍሪካ ግዙፉ የሆነውን ግድብ በጥቂት ወራት ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነም ገልጸዋል።

በአቡዳቢ እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በግድቡ ማጠናቀቂያ ንቅናቄ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያስችል ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱንም ጠቁመዋል።

በሰባቱም ኤምሬቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንደተለመደው ድጋፋቸውን በማድረግ ከሀገራቸው ጎን እንዲቆሙ ጥሪ ማስተላለፋቸውን የኤምባሲው መረጃ አመላክቷል።

Exit mobile version