ስፓርት

አትሌት ድርቤ ወልተጂ አሸነፈች

By ዮሐንስ ደርበው

April 06, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጃማይካ እየተካሄደ በሚገኘው ግራንድ ስላም ትራክ ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር አሸንፋለች።

አትሌት ድርቤ ርቀቱን 4:04.51 በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች።

አትሌቷ በ800 ሜትር 2ኛ የወጣችበት ውጤት ተደምሮ በአጠቃላይ ያገኘችውን ነጥብ 20 ማድረሷን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል።