አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጀርመን በርሊን በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ አሸንፈዋል፡፡
በወንዶች የተካሄደውን የግማሽ ማራቶን ውድድር ያሸነፈው አትሌት ገመቹ ዲዳ፤ ርቀቱን በ58 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡
እንዲሁም በሴቶች አትሌት ፎትየን ተስፋይ የቦታውን ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር አሸንፋለች፡፡
ርቀቱን ለማጠናቀቅም 1 ሠዓት ከ3 ደቂቃ ከ35 ማይክሮ ሰከንድ ፈጅቶባታል፡፡
በዚሁ የውድድር መርሐ-ግብር የተሳተፉት አትሌት ፍታው ዘርዓይ እና ዓለምአዲስ እያዩ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡