አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተለያዩ ሹመቶችን መስጠቱን አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት፦
- አቶ ቻም ኡቦንግ – የክልሉ አካባቢና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ
2.አቶ ኮንግ ጆክ – የክልሉ ከተሞች ፕላን ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር
3.አቶ ሙሴ ጋጄት – የክልሉ መስኖና ቆላማ ቢሮ የመስኖ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
4.ወይዘሮ ታቢታ ኡሪያሚ – ከተማ መሠረተ ልማት ቢሮ የመሰረተ ልማት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ
5.ኢንጂነር ጓነር ጆክ – ከተማ መሠረተ ልማት ቢሮ የከተማ ልማት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ
6.አቶ ቦት ጋች – የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ
7.ዶክተር ሞክ ያንግዶንግ – የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ምክትል ቢሮ ኃላፊ
8.ወይዘሮ ኛልዊት ፓል – የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር
9.አቶ ደሳለኝ ብሩ – የኢኖቬሽን ቴክ/ኮሚ/አይ ሲ ቲ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር
10.አቶ ኒያል ቶት – ኦፔኖ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዲን
11.አቶ ኮንግ ጋች – የገጠር መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር
12.አቶ ኡኬሎ ኡማን – የክልሉ የዳያስፖራ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
13.አቶ ጋርዊች ጋች – የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ የኢነርጂ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ
14.አቶ አቦር አሌክስ – የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሆነው መሾማቸው ተገልጿል፡፡
ሹመት የተሰጣቸው አመራሮች በትምህርት ዝግጅታቸው፣ በአመለካከት ህብረ ብሔራዊነት ወንድማማችነት/ እህትማማችነት፣ የስራ ልምድና አፈፃፀም፣ የመንግስት ወይም የፓርቲ ተልዕኮን ማስፈጸም የሚችሉና በህገ-መንግስት የበላይነት የሚያምኑ መሆናቸውን የርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡