የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ክልል 1 ሺህ 402 የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች ሊያስረክብ ነው

By Yonas Getnet

April 07, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል 1 ሺህ 402 የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች በዛሬው ዕለት በሻሸመኔ ከተማ እንደሚያስረክብ አስታውቋል፡፡

ትራክተሮቹን የሚረከቡት አርሶ አደሮች፣ የህብረት ሥራ ማህበራትና ዩኒየኖች ለክልሉ መንግስት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ሲሆን ÷ ቀድመው የቆጠቡ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

ትራክተሮቹ በኬኛ የግብርና መሳሪያዎች ማምረቻና ጠቅላላ ንግድ ሃላፊነቱ የተወሰነ ድርጅት በሀገር ውስጥ የተገጣጠሙ ናቸው ተብሏል።

ትራክተሮቹ የክልሉ መንግስት የግብርና ሜካናይዜሽንን ለማስፋፋት ለያዘው ውጥን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸው መጠቆሙን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡