የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ክልል 1 ሺህ 402 የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች አስረከበ

By Mikias Ayele

April 07, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል 1 ሺህ 402 የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች በሻሸመኔ ከተማ አስረክቧል፡፡

ትራክተሮቹን የተረከቡት አርሶ አደሮች፣ የኅብረት ሥራ ማኅበራትና ዩኒየኖች፤ ለክልሉ መንግሥት ባቀረቡት ጥያቄ ቀድመው በቆጠቡት መሠረት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ትራክተሮቹ የክልሉ መንግስት የግብርና ሜካናይዜሽንን ለማስፋፋት ለያዘው ውጥን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸው መገለጹን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡