የሀገር ውስጥ ዜና

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሥራ አመራር ቦርድ መልማይ ኮሚቴ ሥራውን ጀመረ

By Adimasu Aragawu

April 08, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሥራ አመራር ቦርድ መልማይ ኮሚቴ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውቋል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢና እና ሁለት አባላትን የሚመለምል ገለልተኛ ኮሚቴ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተቋቁሞ ሥራ መጀመሩም ነው የተገለጸው።

ኮሚቴው ግልጽና አወዳዳሪ በሆነ አካሄድ እጩዎችን ለማቅረብ የእጩዎች ጥቆማ ጥሪ በዛሬው ዕለት ለሕዝብ፣ ፖለቲካ ድርጅቶችና ሲቪል ማኅበረሰብ አቅርቧል።

ጠቋሚዎች የተጠቋሚዎች መግለጫን በተዘጋጀው ፎርም በመሙላት ጥቆማቸውን ከሚያዚያ 1 እስከ ሚያዚያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በኢሜይል፣ ዋትስአፕ፣ ቴሌግራምና ፖስታ አማራጮች ለመልማይ ኮሚቴ ማቅረብ እንዳለበት ጥሪ አቅርቧል።

በሰለሞን ይታየው