የሀገር ውስጥ ዜና

ተፋሰሶችን ለመጠበቅ የጋራ ዕቅድ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

By Adimasu Aragawu

April 08, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ተፋሰሶች ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ በመሆናቸው ለመጠበቅና ለመንከባከብ የተቀናጀ የጋራ ዕቅድ እንደሚያስፈልግ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስገነዘበ፡፡

በሦስቱ ተፋሰሶች የሚተገበር “ብራይት” የተሰኘ የተቀናጀ የተፋሰስ አሥተዳደር ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ተካሂዷል።

የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ አብርሃ አዱኛ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የተቀናጀ የተፋሰስ አሥተዳደር ፕሮጀክት በዓባይ፣ አዋሽ እና የተከዜ ተፋሰሶች ላይ ይተገበራል፡፡

የተፋሰስ አሥተዳደር ፕሮጀክቱ 11 ክልሎች፣ 71 ዞኖች እና 724 ወረዳዎችን ያቀፈ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በኔዘርላንድ ኤምባሲ እና በአውሮፓ ኅብረት የገንዘብ ድጋፍ፣ በውኃና መሬት ሀብት ማዕከል፣ በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባሉ የዓባይ፣ አዋሽ፣ የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች፣ ተከዜ እና ኦሞ ጊቤ የተፋሰስ አሥተዳደር ጽሕፈት ቤት የሚተገበር ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡

በተካልኝ ኃይሉ