አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ህዝብ ላሳየኝ ክብር እና ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አለኝ ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ።
አቶ ጌታቸው ረዳ የሁለት ዓመት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ኃላፊነታቸውን በይፋ ማስረከባቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ አመልክተዋል።
በኃላፊነት ቆይታዬ የትግራይ ህዝብ ላሳየኝ ክብር እና ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አለኝ ያሉት አቶ ጌታቸው÷ ህዝባችን ወደ ተሻለ ሁኔታ እንዲመለስና ሁለንተናዊ ፍላጎቱ እንዲሟላለት የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ ብለዋል።
የሰላም እና የለውጥ ፍላጎቶች እንዳይሰናከሉ ትግላችንን እናጠናክር ሲሉም ገልጸዋል።