Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመከላከያ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማና የሚበረታቱ ናቸው – አይሻ መሃመድ (ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በመከላከያ ሠራዊት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማና የሚበረታቱ መሆናቸውን የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) ገለጹ፡፡

የመከላከያ ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሯ አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) በዚሁ ወቅት፥ በተቋሙ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማና የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በአራተኛው ሩብ ዓመት ይበልጥ የተሻለ የእቅድ አፈፃፀም ውጤት ለማስመዝገብ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የተቋሙን ታላላቅ ግቦች መሰረት ያደረገ የእቅድ አፈፃፀም ማስመዝገብና የመከላከያን ሙሉ አቅም ተጠቅሞ ወደ ውጤት ለመቀየር ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ መግለፃቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

ሠራዊቱን ከአዳዲስ ቴክኖሎጂ ጋር በማዋሀድ በአስተማማኝ መልኩ ሠላምን እንዲጠብቅ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ተግባራት መከናወናቸውም በሪፖርቱ ላይ ተመላክቷል፡፡

የኢንዱስትሪዎችን አቅም በማሳደግ፣ ወታደራዊ ዲፕሎማሲውን ከፍ በማድረግ፣ የሰው ሀብት አቅምን በማደራጀትና በማዘመን፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ስልጠናዎች የመስጠት ሥራዎች መሰራታቸውም ተጠቁሟል።

Exit mobile version