አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ጆሽዋ ታባን እና የካናዳ የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ቤንማርክ ዴንዴር ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ የኢትዮጵያ እና ካናዳን ታሪካዊ ግንኙነት በይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያግዝ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡
በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ወቅታዊ አተገባበር ዙሪያም ገለጻ ማድረጋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
አምባሳደር ጆሽዋ ታባን በበኩላቸው፤ ካናዳ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በካናዳ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተመሩ ልዑኮች በኢትዮጵያ ተከታታይ ጉብኝቶች ማድረጋቸውን ተቅሰው፤ ይህም የሀገራቱን ግንኙነትነ በይልጥ ለማጠናከር ያለውን ፍላጎት ያሳያል ብለዋል፡፡
በውይይታቸው ላይ በሀገራዊ የሁለትዮሽ እና ቀጣዊ ጉዳዮች ላይም መምከራቸው ተገልጿል፡፡