አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ለናይጄሪያ የመከላከያ ኃይል ከፍተኛ ልዑክ የኢትዮጵያን የልማት ተሞክሮ አጋሩ።
49 አባላትን ያካተተው የናይጄሪያ መከላከያ ኃይል ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የሥራ ጉብኝት አድርጓል።
በጉብኝቱ ወቅት ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፤ በዘላቂ ልማት፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚ መስኮች ኢትዮጵያ የምትሰራቸውን ሥራዎች በተመለከተ ገለጻ በማድረግ ተሞክሮዋን አጋርተዋል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት ለተደረገው ገለጻ እና አቀባበል ምስጋና ማቅረባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡