Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ እና ብራዚል የቢዝነስና ኢንቨስትመንት ፎረም መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እና የብራዚል የቢዝነስና ኢንቨስትመንት ፎረም በብራዚል ሳኦፖሎ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በፎረሙ መክፈቻ ላይ በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ፣ የብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር አንቶኒዮ ሴዛር፣ የኢትዮጵያና ብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች እና የሁለቱ ሀገራት የንግድ ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።

ፎረሙ የኢትዮጵያን እምቅ የኢንቨስትመንት፣ የንግድ እና ቱሪዝም አቅም ማስተዋወቅ ያለመ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ሁነቱ የኢትዮጵያ እና ብራዚልን የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር የማጠናከር ፋይዳ እንዳለውም ገልጿል።

የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አቅም የሚያስተዋውቅ ፎረም በየካቲት ወር 2017 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በተገኙበት በብራዚሊያ መካሄዱን በብራዚል የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አስታውሷል።

Exit mobile version