Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው ዕለት ባካሄደው 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ስብሰባ አራት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በዚህም መሰረት፡-

1ኛ. በፕላንና ልማት ቢሮ እና በትምህርት ሚኒስቴር በጋራ ተጠንቶ የቀረበውን ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለው አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር በመሆን በአካባቢው ያሉትን አገልግሎቶች አካቶ የትምህርት፣ የምርምር፣ የእውቀት እና የባህል ልህቀትን በከተማዋ ለማሳደግ በሚያስችል አግባብ የቀረበ በመሆኑ ካቢኔው ተወያይቶ የመንደር ምስረታውን ውሳኔ አፅድቋል፡፡

2ኛ. የምግብ ሥርዓትና ኒውትሪሽን ምክር ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።

3ኛ. የአደጋ ስጋት አመራር ምክር ቤትና የአደጋ ዝግጁነት ፈንድ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ካቢኔው ተወያይቶ ዉሳኔ አስተላልፏል፡፡

4ኛ. በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቀረበውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶች፤ የመሬት ምደባ ጥያቄዎች አስመልክቶ ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version