አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ24 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያለው 3 ሺህ 700 ኩንታል የቡና ምርት መያዙን አስታወቀ፡፡
ቡናውን ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ ለማስገባት እና ከአዲስ አበባ ወደ ባሕርዳር ለመውሰድ በተሽከርካሪዎች እንደተጫነ መያዙን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡
ኮንትሮባንድ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ ተፅዕኖ በመገንዘብ ሕብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት እያደረገ ስላለው ትብብር ያመሠገነው ፖሊስ፤ ይህን ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል፡፡