አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘቷን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።
የሚኒስቴሩ እና ተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እየገመገሙ ነው፡፡
በዚሁ ወቅት ሚኒስትሩ፤ በኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፈቃድ ለ2 ነጥብ 6 ሚሊየን ተገልጋዮች አገልግሎት መሰጠቱን እና 2 ነጥብ 2 ሚሊየን የድረ-ፍቃድ ኢንስፔክሽን መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
374 ተጨማሪ የሰንበት ገበያዎች ተቋቁመዋል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ከወጪ ንግድ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር መገኘቱን ጠቅሰው፤ ይህም በሀገሪቱ ወጪ ንግድ ታሪክ ከፍተኛው ነው ብለዋል፡፡